713-484-5530 ecfc@ecfchouston.org
ECFC Choir A
ECFC Choir B
Azeb & Worship Team
Worship Team
previous arrow
next arrow

Worship

ብሉይ ኪዳን “ያመልከኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ” ብሎ እግዚአብሔር የተናገረውን፤ እንዲሁም ደግሞ በአዲስ ኪዳን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “..ነገር ግን በእውነት የሚሰግዱ ለአብ በመንፈስና በእውነት የሚሰግዱበት ጊዜ ይመጣል አሁንም ሆኖአል፤ አብ ሊሰግዱለት እንደ እነዚህ ያሉትን ይሻልና። “ የሚለውን እውነት በመረዳት አምልኮ በ ኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ሕብረት ቤተ ክርስቲያን በሂውሰተን ትልቅና ክቡር ስፍራ አለው። በቤተ ክርስቲያናችን በሚገኙ “ሀ” ና “ለ” የመዘምራን አገልግሎትና በቅርቡም በተቋቋመው የአምልኮ ቡድን አማካይነት ሰፊ የአምልኮ አገልግሎት ይካሄዳል። በነዚህ የአምልኮ አገልግሎቶች ውስጥ ያሉ አባላት ቤተ ክርስቲያኒቱ በቋሚነት ከምትሰጠው ሳምንታዊ ፕሮግራሞች ሌላ በዓመቱ ውስጥ በሚካሄዱት ልዩ ልዩ ኮንፈረንሶች ላይ ትልቅ ተሳትፎ ያደርጋሉ። በዓለም ዚሪያ ባሉ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ይህንን አገልግሎት ለሚሰጡ ሁሉ የእግዚአብሔር ፀጋ ይብዛላችሁ እንላለን።

ministries

Family Ministry

የባለትዳሮች ህብረት አገልግሎት በኢትዮጵያዉያን ክርስቲያኖች ኅብረት ቤተክርስትያን አስተዳደር መመሪያና መተዳደሪያ ደንብ መሰረት፤ የአጥብያ ቤተክርስቲያን አካል ሆኖ የሚሰራ ነዉ ። ዋና የአገልግሎቱ ትኩረት ባልና ሚስት እርስ በእርስ ሊኖራቸዉ የሚገባዉን ግንኙነት በእግዚአብሔር ቃል መሰረት በፍቅር፤ በመከባበርና አንዱ ሌላዉን ለመርዳት (to understand each other) በመጣርና በመተሳሰብ ፤ በመደጋገፍ ላይ እንዲመሰረትና እንዲያድግ ማበረታታት ነዉ ።

አገልግሎቱ አጥቢያ ቤተክርስተያንዋ የተሰጣትን ዋና የማስተማር ተልእኮዋን ቤተሰብን በተመለከተ መስክ (topics/subject) ረገድ ለመተካት ሳይሆን፤ ስራዋን በማገዝና በመ ደገፍ እንደ አንድ የአካልዋ ክፍል ለተልኮዋ ስኬት መተባበር ነዉ ።

አገልግሎቱ በተለይ የታወቀበትና በየዓመቱ በጉጉት በብዙዎች ዘንድ የሚጠበቀዉ ‘በፌበሪዎሪ’ አጋማሽ ላይ የሚ ኪያሄደዉ “የፍቅረኞች ጊዜ” ነዉ ። በዚህ ጊዜ ባለትዳሮች በሚኖራቸው የሕብረት ጊዜ ትዳርን በተመለከተ የተለያዩ ትምህርቶች ይሰጣቸዋል።

እንደዚሁም በየጊዜው ባለትዳሮችን በተመለከተ፥ ትምህርታዊ አውደ ጥናቶችን (workshops) በማዘጋጀት፤ በቤተሰብ ነክ ጉዳዮች ላይ እግዚአብሔርን በማገልገል የተሰማሩትን ወንድሞችና እህቶችን ከዉጪም ሆነ ከዉስጥ በመጋበዝ የማነቃቂያና የማበረታቻ ፕሮግራሞችን ያስተባብራል ።

ዶክተር አባተ ወልደቂርቆስ እና ወይዘሮ መዓዛ

የአገልግሎቱ ዋና አስተባባሪዎች

ወይዘሮ ሒሩት በየነ እና አቶ ዮናስ

የአገልግሎቱ ዋና አስተባባሪዎች

ministries

Children Ministry

ቤተ ክርስቲያናችን ለልጆች ልዩ እንክብካቤና አገልግሎት አላት። ስለዚህ፥ በዚህ ዘርፍ ለማገልገል የተሰጡትን አስተማሪዎች በመጠቀም ዕድሜያቸው ከአሥር ወር ጀምሮ ያሉትን ልጆች፥ በእድሜና በክፍል ደረጃ በተዘጋጀው መጽሐፍ በመደገፍ የእግዚአብሔርን ቃል ታስተምራለች።

 ስለ ልጆች የሰንበት ትምሕርት በጥልቀት መረዳት ከፈለጉ ወይም በአገልግሎቱ ተካፋይ መሆን ከፈለጉ በስልክ ወይም ስማቸው ከዚህ በታች የተጠቀሱትን የሕጻናት የሰንበት ትምህርት አገልግሎት መሪዎች በግል ለማናገር ይችላሉ።

ministries

Virtuous Women Ministry

የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ኅብረት ቤተ ክርስቲያን በሂውስተን የሴቶች ኅብረት የተቋቋመው ቤተ ክርስቲያኒቱ ከተመሠረተችበት ጊዜ ጀምሮ ነው። ይህ ኅብረት ባለፉት ዓመታት ሴቶችንና ቤተ ክርስቲያኒቱን በአጠቃላይ በተለያዩ መንገዶች በመደገፍና በማገልገል ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል። አሁን ደግሞ፣ ይህ ኅብረት ፦

      “ ልባም ሴትን ማን ሊያገኛት ይችላል? ዋጋዋ ከቀይ ዕንቁ ይበልጣል” (ምሳ.31፡10)

የሚለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል መሪ በማድረግ “ልባም ሴት የእህቶች አገልግሎት” በሚል ስያሜ ከምንጊዜውም ይልቅ በተጠናከረ መልኩ ተደራጅቶ በቤተ ክርስቲያኒቱና ባካባቢዋ የሚገኙትን ሴቶች በማገልገል ላይ ይገኛል።

ministries

Evangelism

The evangelism ministry at ECFC emphasizes outreach and spreading the message of Christianity. It actively engages in various areas to share the teachings of the faith and bring more people to Christ.

ministries

Media Ministry

የሚዲያ አገልግሎት ዋና ዓላማው የተመሰረተው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 28፤ 19-20
ለደቀ መዛሙርቱ ዛሬ ደግሞ በእርሱ ላመንን ለእኛ በሰጠው ታላቅ ትዕዛዝ ላይ ነው።

“ እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤…”

በዚህም መሰረት የሚዲያ አገልግሎት የዘመኑን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ቪዲዮ ኦውዲዮ በየሳምንቱ ዘወትር እሁድ በተጨማሪም ደግሞ በተለያዩ ጌዜያት በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ የሚካሄዱ ኮንፍረንሶች እና የተለያዮ የኅብረት ፕሮግራሞችን ወደ ቤተክርስቲያኒቱ ለሚመጡም ሆነ ከዓለም ዙሪያ በኢንተርኔት ፕሮግራሙን ለሚከታተሉ ምዕመናን በቀጥታ በድምፅ እና በምስል አቀነባብሮ በማስተላለፍ፤ የሚተላለፈውን በመቅረፅ፤ የተቀረፀውን በዚሁ አገልግሎት በሚደገፍ ድረ ገጽ በኩል በቅርብም ሆነ በሩቅ ላሉ የምስራቹን ዜና ያልሰሙ ሰዎች እንዲሰሙና እንዲድኑ የሰሙትና የዳኑት ደግሞ ደግሞ እንዲታነፁ እውነኛው የእግዚአብሔር ቃል እንዲደርሳቸው ማድረግ ነው።

Contact

  • Our Number
    713-484-5530

  • Our Email
    ecfc@ecfchouston.org
  • Our Address
    401 Present Street
    Missouri City, TX 77489

Connect 

 

New Here? Fill out the membership form